ለክለባችን እድገት የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ ነው፡፡

የአዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በ2007 ዓ.ም በፕሪሚየር ሊጉ ተሳትፎ ቀጣይነት እና መሰረት ባለው መልኩ ውጤታማ ለመሆን የክለቡን የስትራቴጂክ እቅድ ከማዘጋጀት ጀምሮ፡ክለቡ ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረው የክለቡ የደጋፊ ማህበር በማቋቋም ደረጃ በደረጃ ህብረተሰቡ በባለቤትነት የሚሳተፍበት እና ተጠቃሚ የሚሆንበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የተለያዩ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ክለባችን እንደማንኛውም በሀገራችን ካሉ ውጤታማ የሆኑ ክለቦች እና በአህጉር አቀፍ ደረጃ ውጤታማ የሆኑ ክለቦች ተርታ ለማደራጀት እና ለማጠናከር የተለያዩ ክለቡ የሚመለከታቸው አመራር አካላት፤ህብረተሰቡ፡ባለሀብቶች የተለያዩ ተቋማት እና ባለድረሻ አካላት የተቀናጀ ስራዎችን የማከናወን ኃላፊነት ይጠበቅባቸወል፡፡ክለባችን በ2007 ጀምሮ የራሱ የሆነ የሦስት አመት ስትራቴጂክ እቅድ በማዘጋጀት፡ክለቡን የኃብት ማሰባሰቢያ ሰነዶች እና የተለያዩ መመሪያዎች እና ደንቦችን በማዘጋጀት ወደ ስራ ለመግባት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

በመሆኑም ከተዘጋጀው የስትራቴጂክ እቅድ ላይ የክለቡን ተልዕኮ፤ራዕይ፤ዕሴት እና ክለቡን በቀጣይነት ውጤታማ ለማድረግ መሰራት የሚገባቸው ስራዎች አንባቢን እና የክለቡ የሚመለከታቸው አካላት እና ደጋፊዎች እንዲረዱት በቀጣይም ከክለቡ ጎን በመሆን የድረሻቸውን እንዲወጡ በአጭሩ ለማስቀመጥ እንሞክራለን፤

Leave Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *