ትኩረት

አለም አቀፍ የእግር ኳስ ክለቦችን የእድገት ሁኔታ ስናይ ሀገሮች ስፖርቱ ከማህበራዊ ጠቀሜታ አልፎ የሀገሮች ፖለቲካዊ እና የማንነት መገለጫ በመሆኑ እና በይበልጥም ለሀገራቸው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ውስጥ ትልቅ አስተዋጽዖ እያደረገ ያለ ዘርፍ መሆኑን በመረዳት ለክለቦች አለማቀፋዊ የክለብ አደረጃጀት እና አሰራር ስርአት በመፍጠር ከመንግስት የገንዘብ ድጎማ አልፈው በየአመቱ ክለቦች የራሳቸውን ቋሚ የገቢ ምንጭ በማዳበር በሀገራቸው ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገት ላይ የራሳቸውን ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ በማድረግ ላይ ሲሆኑ የእያንዳነዱ ክለብ የተወዳዳሪነት እና ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ ሚስጥር ሀገራቶች የረጅም አመታት ቀጣይነት ያለው ስራ በመስራት ክለባቸውን ህዝባዊ መሰረት እንዲኖራቸው በማድረግ እና እያንዳንዱ ክለብ ተተኪ ታዳጊ ወጣቶችን ለማፍራት የራሳቸውን አደረጃጀት እና አሰራር በመፍጠር ነው፡፡
በአንጻሩ የክልላችንን የእግር ኳስ ክለቦች ተጨባጭ ሁኔታ ሲታይ በተለያዩ ዓመታት ክለቦች ተቋቁመው በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቆይታ ውስጥ ተሳትፎ ያደረጉ ቢሆንም በአጠቃላይ የክልላችን የአብዛኛው ክለቦች ብሎም የአዳማን ክለብ ጨመሮ በ2005 ከፕሪሚየር ሊጉ መውረድ እና መዳከም በሁሉም ደረጃ በአስፈጻሚ አካላት ተመሳሳይ ግንዛቤ አለመኖር፤የማስፈጸም አቅም ብቃት ውስንነት እና ለክለቦች መሠረት የሆኑት በቂ የስፖርት መሰረተ ልማት አቅርቦት አለመኖር፤ክለቦች የመንግስት ፖሊሲ በሚያዘው አቅጣጫ ህዝባዊ አደረጃጀት ኖርዋቸው ክለቡን በተደራጀ መልኩ በሰው ኃይል፤በቁሳቁስ እና የአሰራር ስርአት ያለመኖር እና በአብዛኛው ከመንግስት የሚመደብላቸው ውስን በጀት ውጪ የራሳቸው የሆነ ቋሚ የገቢ ምንጭ የሚፈጥሩበትን አሰራር ያለመኖር ዋና ዋና ቁልፍ ችግሮች እንደሆኑ ከተደረጉ ጥናቶች መገንዘብ ይቻላል፡
በመሆኑም የክለባችንን ዘላቂ ውጤት ባለው መሰረት ላይ ለመጣል በመነሻ በሀገራችን የሚገኙ የተሻለ ህዝባዊ አደረጃጀት፤አሰራር ስርአት እና የራሳቸው ቋሚ የገቢ ምንጭ ለመፍጠር የተሻለ ተሞክሮ ያለቸውን በመውሰድ እና ስራ ላይ በማዋል በመቀጠልም ውጤታማ የሆኑ አለማቀፍ የክለቦች አደረጃጀት እና አሰራር ስርዓት በመውሰድ ደረጃ በደረጃ በሂደት ስራ ላይ ለማዋል አንድ ብለን ስንጀመር እና ትኩረት ሰጥተን ስንተገብር ነው፡፡

የክልላችን ህዝብ ብሎም የክለባችን ደጋፊ የሚፈለገውን ውጤት ቀጣይነት እና መሰረት ባለው ደረጃ በሀገር አቀፍ ብሎም በአህጉር አቀፍ ተፎካካሪ እና ተወዳዳሪ ለመሆን የአዳማ እግር ኳስ ክለብ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ እንዲመለስ ሁሉም አካላት ትኩረት በማድረግ እና በመረባረብ በተሰራበት ደረጃ የነበሩንን ችግሮች ደረጃ በደረጃ በመፍታት፤በከተማችን እንዲሁም በክልላችን ያሉትን መልካም አጋጣሚዎችን በመጠቀም ብሎም በከተማችን የሚገኙ በእግር ኳሱ ክህሎት ያላቸው ወጣቶችን በማደራጀት እና በማሳተፍ ሁሉም የሚመለከተው የመንግስት አስፈጻሚ አካል፤ህብረተሰቡ፤ልማታዊ ባለኃብቶች፤መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በተቀናጀ መልኩ ድርሻቸውን በመወጣት ክለባችንን ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩበት ይገባል፡፡
ይህንንም ለማሳካት የአዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ እንደ ተቋም በሁሉም መመዘኛ በአደረጃጀት፤በሀብት እና በተወዳዳሪነት ቀጣይነት እና መሰረት ባለዉ ደረጃ ማደራጀት እና ማጠናከር አስፈላጊ እና ሊተኮርበት የሚገባው ጉዳይ ሲሆን፤ ክለባችንን ወደሚፈለገው ውጤት እና ደረጃ ለማሸጋገር ሰፊ ስትራቴጂክ ስራዎችን መስራት የሚጠበቅ ሲሆን ከነዚህም ዋንኛው እና የመጀመሪያው ሰፊ የህብረተሰብ ንቅናቄ መፍጠር፤የአዳማ ከተማ ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን አብዛኛውን የክልላችንን ማህበረሰብ በስፋት ሊያሳትፍ የሚችል፤በሀገራችን እና ከሀገር ውጪ በክለቡ የመሳተፍ ፍላጎት ያለውን አብዛኛውን ማህበረሰብ በቀጥታ በባለቤትነት ሊያሳተፍ እና ተጠቃሚ ሊያደርግ የሚችል እና ቀጣይነት ባለው ክለቡን ወደ ተሻለ ደረጃ ማሸጋገር የሚችል ጠንካራ ህዝባዊ መሰረት ያለው የደጋፊ ማህበር የሚቋቋምበትን እና ወደ ተግባር የሚቀየርበትን ሁኔታ ማመቻቸት ወሳኙ የሚተኮርበት ጉዳይ ነው ፡፡

Leave Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *