ከደጋፊዎች የአዳማ እንግዳ፡፡

በማንኛውም የእግር ኳስ ክለብ እንቅስቃሴ እና ውጤት ዙሪያ የክለብ ደጋፊዎች ሚና ይኖራል፡፡ያለ ክለብ ደጋፊዎች ተሳትፎ አንድ ክለብ የተፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ አስቸጋሪ ነው፡፡በይበልጥ ውጤታማ የሆኑ ክለቦች በብዛት እና በጥራት ክለቡን በቀጣይነት የሚደግፉ ደጋፊዎች ያላቸው ክለቦች ናቸው፡፡አለማቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ስለ ደጋፊዎች ሲጠቅስ ደጋፊዎች ’የእግር ኳስ ጨዋታ ውበት ናቸው’ ነው የሚላቸው፡፡የተለያዩ የአፍሪካ በይበልጥም የአውሮፓ ሀገራት ክለቦች በክለብ ስር ባለ የደጋፊ ማህበራት ስር ተመዝግበው እና እውቅና አግኝተው ክለባቸውን ቀጣይነት ባለው መልኩ በተለያየ ሁኔታ በመደገፍ እንቅስቃሴ የሚያደረጉበት ሁኔታ እንዳለ ይታወቃል፡፡በሀገራችንም ደጋፊዎች ክለባቸውን በተለያየ መልኩ በመደገፍ ከሚታወቁት ክለቦች ውስጥ ለመጥቀስ የኢትዮጵያ ቡና፤ቅድስ ጊዮርጊስ፤ወላይታ ዲቻ፤ሲዳማ ቡና እና አርባ ምንጭን መጥቀስ ይቻላል፡፡
የአዳማ እግር ኳስ ክለብ የራሱ የሆነ የደጋፊ ማህበር በማቋቋም በተለያየ ጊዜ የተወሰኑ እንቅስቃሴዎችን ያደረገበት ሁኔታ እንዳለ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በዚህም ወደፊት ክለባችን ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረው አብዛኛውን ማህበረሰብ በቀጥታ በባለቤትነት በክለቡ ተሳታፊ በማድረግ ቀጣይነት እና መሰረት ባለው መልኩ ክለቡን በአደረጃጀት፤በሀብት እና በተወዳዳሪነት ወደ ተሻለ ደረጃ ማሸጋገር የሚያስችል ጠንካራ ህዝባዊ መሰረት ያለው የደጋፊ ማህበር ማቋቋም ወሳኝ ሲሆን እያንዳንዱ ማህበረሰብ ከዚህ በፊት ከሚያደርገው ተሳትፎ በላቀ ደረጃ የክለቡ ደጋፊ አባል በመሆን በማህበሩ ውስጥ የራሱን አስተዋጽዖ ማድረግ የሚጠበቅበት ይሆናል፡፡
በአዳማ እግር ኳስ ክለብ የደጋፊዎችን ሁኔታ ስናነሳ ክለቡን ወደ ተሻለ ደረጃ እነዲሸጋገር እና ውጤት እንዲያስመዘግብ የበኩላቸውን የተወጡ የክለቡ ደጋፊዎች በይበልጥም ከአዳማ ከተማ የሚገኙ ብዛት ያላቸው ደጋፊዎች ይገኛሉ፡፡
ከነዚህም ደጋፊዎች በዚህ እትም የምናነሳቸው እና ተጋባዥ የምናደርጋቸው የአዳማ ክለብ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ፤ ከልጅነት እድሜያቸው አንስቶ ለረጅም አመታት ክለቡ በሚያደርገው የተለያዩ ውድድሮች ላይ በመገኘት፤ክለቡ በተለያየ ወቅት ችግር ሲገጥመው ከችግሩ እንዲወጣ በመደገፍ እና በማበረታት ከሚታወቁት መካከል ደጋፊ ቡጡሽ እና ትርፉን በዚህ እትም ለመጋበዝ ወደናል፡፡ሌሎችንም በቀጣይ መጽሄታችን ደረጃ በደረጃ የምንጋብዛቸው ይሆናል፡፡

Leave Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *