የአዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በኃገራችን ከተቋቋሙ አንጋፋ ክለቦች  መካከል አንዱ ሲሆን ክለቡ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በሀገር ደረጃ እንደ ክለብ አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ በተለያዩ አመታት ሀገርን በመወከል በብሄራዊ ቡድን ታቅፈው ከፍተኛ ደረጃ የደረሱ ስፖርተኞችን በማፍራት የበኩሉን አስተዋጽዖ ያበረከተ ክለብ ነው፡፡ከዚህም በተጨማሪ በክለቡ በስፖርተኝነት አሳልፈው ከፍተኛ የአሰልጣኝነት ደረጃ የደረሱ እና በተለያዩ የሀገራችን ታወቂ እና አንጋፋ ክለቦችን በማሰልጠን ከፍተኛ ውጤት ከማስመዝገብ በተጨማሪ በተለያዩ ሀገሮች አሰልጣኝ በመሆን ከፍተኛ ደረጃ የደረሱ የስፖርት ባለሞያዎችን ማፍራት የቻለ ክለብ ነው፡፡

cropped-scan0026የአዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ታሪካዊ አመሰራረቱ እና እሰከ አሁን ያለፈባቸውን ሂደቶች የሚተርክ በዶክመን ደረጃ ይሁን በጽሁፍ የተቀመጠ ማስረጃ ባይኖርም ክለቡ ከምስረታው ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ባሳለፈባቸው አመታት በአመራርም ደረጃ፤በተጨዋችነት እና በደጋፊነት አብረውት የተጓዙ ብዛት ያላቸው ሰዎች በቂ ሙሉ ማስረጃ በማጠናከር የክለቡን ታሪክ  ወደፊት ማጠናከር የሚያስችል አቅም ቢኖርም ለዚህ መጽሄት ዝግጅት እንዲረዳ ከተወሰኑ ከክለቡ ጋር ከምስረታ ጊዜ አንስቶ አስከ አሁን በክለቡ ድረሻ ያለቸው ሰዎች የተወሰነ ማለቱ ወደፊት የክለቡን ታሪክ በስፋት በተቀናጀ መልኩ ለማስቀመጥ ለመነሻ እና ለዋቢነት እንscan0031-1024x672ዲረዳ በአጭሩ በዚህ መጽሄት ላይ ማስቀመጥ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

የክለቡንም ታሪካዊ ዳራ በዚህ መጽሄት ላይ በአጭሩ ለማስቀመጥ ክለቡ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን በክለቡ በተለያየ ተሳትፎ ያደረጉ እና እያደረጉ ካሉት
መካከል ለመጥቀስ አሰልጣኝ ውበቱ አያሌው፤አቶ ግርማ ታደሰ፤ሱራፌል ይልማ፤ይታገሱ እንዳለ፤ደጋፊ ዘርፉ መሸሻ እና የተለያዩ ሰዎች  በዚህ አጭር ታሪካዊ ዳራ ላይ በማሳተፍ እና አስተያየት እንዲሰጡ በማድረግ እንደሚከተለው ለማቅረብ ተችሏል፡፡

የአዳማ ከተማ በወቅቱ በምስራቅ ሸዋ ዞን ስር ከሚተዳደሩ ከተሞች አንዱ ሲሆን በ1986 ዓም በምስራቅ ሸዋ ዞን በአመቱ በሚደረገው ሻምፖዮና ላይ ለመሳተፍ በወቅቱ በከተመዋ ከሚገኙ 6 ቀበሌዎች ውስጥ የተውጣጡ ስፖርተኞችን በመምረጥ የቡድኑ አባላት በራሳቸው በከተማዋ ያሉ ባለኃብቶችን በማስተባበር እና እርዳታ በመጠየቅ በተገኘ የተወሰነ ገንዘብ የስፖርት ትጥቆች እና scan0029-1024x669ቁሳቁሶችን በማሟላት ለመጀመሪያ ጊዜ በ1986 ዓም የምስራቅ ሸዋ ዞን የዙር የክለቦች ውድድር ላይ በመሳተፍ በአመቱም ሻምፒዮና ለመሆን ችሏል፡፡

በ1987 ዓም የቡድኑ አባላት በራሳቸው በውድድር መሳተፍ አስቸጋሪ እና ከአቅም በላይ በመሆኑ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልል ድረስ በመሄድ ለከተማው የድጋፍ ደብዳቤ እንዲጻፍላቸው በማድረግ በዚህም መነሻ የከተማ መስተዳድሩ ለመጀመሪያ ጊዜ በአመቱ 40፣000.00/አርባ ሺህ ብር/በመመደብ እና ሌሎች የክለቡ ደጋፊዎች እና የክለቡ አባላት በከተማው የሚገኙ ባለኃብቶችን በማስተባበር የአመቱ የምስራቅ ሸዋ ዞን የጥሎ ማለፍ እና የአሸናፊዎች አሸናፊ መሆን ችሏል፡፡

በዚህም መነሻ በ1987 ዓም የአዳማ ከነማ የአመቱ የምስራቅ ሸዋ ዞን ሻምፒዮና በመሆኑ በ1988 ዓም ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኦሮሚያ አንደኛ ዲቪዚዮን ወድድር ሊቀላቀል ችሏል፡፡በዚህም አመት ክለቡን በይበልጥ ለማጠናከር ከተማ መስዳድሩ 78000.00/ሰባ ስምንት ሺህ/ብር በመመደብ ለመጀመሪያ ጊዜ ከከተማው ውጭ ከሚገኙ ክለቦች ከአሰላ ብቅል ፋብሪካ እና ከወንጂ ስኳር ፋብሪካ ክለቦች አዳዲስ ሰፖርተኞችን በማስፈረም በአመቱ በተደረገ የኦሮሚያ አንደኛ ዲቪዚዮን ሻምፒዮና ላይ ሁለተኛ ደረጃ በመሆን አጠናቋል፡፡በዚሁ አመት ሐረር ከተማ በተደረገ የኦሆዲድ 5ኛ አመት ምስረታ በዓል ውድድር ላይ ከተካፈሉት ሀረርጌ ምርጥ፤ሙገር ሲሚንቶ እና አሰላ ምርጥን በማሸነፍ የውድድሩ ሻምፒዮና ሆኗል፡፡

በ1989 ዓም የከተማ መስተዳድሩ ክለቡን ለማጠናከር በአመቱ 100000.00/አንድ መቶ ሺህ ብር / በመመደብ ለተጨዋቾች ክፍያ ከባለፉት አመታት scan0032-150x150ለተጨዋቾች ትልቁን ወርኃዊ ደሞዝ 600.00/ስድስት መቶ ብር/በመክፈል በክለቡ መነቃቃት በመፍጠር ከምንግዜውም በላይ ጠንካራ እና ተፎካካሪ ክለብ በመመስረት በአመቱ በተሳተፈበት የኦሮሚያ የዙር እና የአሸናፊዎች አሸናፊ በመሆን ለመጀመርያ ጊዜ ኦሮሚያን በመወከል ሀገር አቀፍ የክለቦች ሱፐር ሊግ ደረጃ ማደግ ችሏል፡፡

በ1990 ዓም ክለቡ በሀገር አቀፍ የክለቦች ሱፐር ሊግ ሻምፒዮና ላይ ከተመደበበት ምድብ ከኢትጵያ ንግድ ባንክ እና ከመብራት ኃይል በመሸነፉ እና አዋሳ ዱቄት እና ደብረ ብርሀን ብርድ ልብስን በማሸነፍ ከምድቡ ሦስተኛ በመውጣቱ ከምድቡ ሳያልፍ በመቅረቱ ተመልሶ ወደ ኦሮሚያ አንደኛ ዲቪዚዮን ሊወርድ ችሏል፡፡

በ1991 ዓም ክለቡን ያለበትን ችግር በመቅረፍ በደነበረበት ሀገር አቀፍ ሱፐር ሊግ ለመመለስ በተደረገ ጠንካራ ስራ የኦሮምያ የአሸናፊዎች አሸናፊ በመሆን ወደነበረበት ለማሳደግ ተችሏል፡፡

በ1992 ዓም ክለቡን በይበልጥ ለማጠናከር ሲባል በተሰራው ስህተት በክለቡ የነበሩትን ጠንካራ እና ልምድ ያላቸውን አሰልጣኞች እና ተጨዋቾች በመቀነሳቸው እና በአብዘኛው በአዳዲስ ስፖርተኞች በመተካታቸው በተደረገው ሀገር አቀፍ ሱፐር ሊግ ከተካፈሉ 12 ክለቦች መካከል ድሬደዋ ጨርቃ ጨርቅን ብቻ በማሸነፉ እና በአመቱ አንድ ክለብ ብቻ ከሊጉ ወደ ታች እንዲወርድ በመወሰኑ 11 ኛ ደረጃ በመያዝ ለጥቂት ከሱፐር ሊጉ ሳይወርድ ቀርቷል፡፡

scan0025-300x196ጊዜው በዚሁ አመት መጋቢት 19/1992 ዓም ቀኑ የገብርኤልን በአል ለማክበር በጠዋት ተጨዋቾች ቤተ ክርስቲያን ደርሰው በመመለስ ፖስታ ቤት አካባቢ ከነበረው አሰብ ሆቴል ሻይ በመጠጣት ላይ እንዳሉ የክለቡ ስድስት ተጨዋቾች ዳንኤል ተክሉ፤መስፍን ላንባሮ፤ብርሀኑ ቃሲም፤ሱራፌል ስዩም፤መስፍን ጌታቸው እና መሐመድ ጀማል ላይ የቦንብ ፍንዳታ አደጋ የደረሰባቸው ወቅት ነበር፡፡የዚህ አደጋ መድረስ አጠቃላይ ክለቡ አባላት እና በክለቡ ደጋፊ ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ እና ሀዘን የተከሰተበት ሂደት ነበር፡፤የክለቡ አስተዳደር ተጎጂ ስፖርተኞች ህክምና እንዲያገኙ ከማድረግ በተጨማሪ በይበልጥም የክለቡ ደጋፊ ህብረተሰቡን በማስተባበር ተጎጂዎች በአጭር ጊዜ አገግመው ወደ ክለቡ እንዲቀላቀሉ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርገዋል፡፡በይበልጥም በወቅቱ ህብረተሰቡን በማስተባበር ከፍተኛ ስራ የሰራው የክለቡ ምንጊዜም እውነተኛ ደጋፊ ዘርፉ ውባለም ስራ የሚዘነጋ አይደለም፡፡

በ1993 ዓም ከተማ መስተዳድሩ ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገብ ፊርማ ገንዘብ በመመደብ ከተለያዩ ክለባት ተጨዋቾችን በመቅጠር አሰልጣኝ በመመደብ በደ ውድድር ቢገባም በዓመቱ ካሉት አስራ ሁለት ክለቦች የሰባተኝነትን ደረጃ በመያዝ ሊያጠናቅቅ ችሏል፡፡

በዚህም ውጤት የተከፉት ተጨዋቾች በ1994 አም ክለቡ በአዲስ አወቃቀር እና አሰልጣኝ እነዲመራ በመደረጉ እና አዳዲስ ተጨዋቾች በመቀየራቸው በአመቱ ከተሳተፉ 12 ክለቦች የ4 ኛነትን ደረጃ በመያዝ የአመቱን ውድድር አጠናቋል፡፡

በ1995 ዓም የነበረውን ውጤት ለማስጠበቅ ከመሄድ ይልቅ በክለቡ አመራር አሰልጣኝ በመቀየር እና የተለያየ ለውጥ በማድረግ በተከሰቱ በክለቡ ውስጥ ችግሮች በዓመቱ ካሉት 14 ክለቦች 13 ኛን ደረጃ በመያዝ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ይሁን እና የክለቡ አመራር እና ደጋፊው ክለቡ ወደታችኛው ሊግ እንዳይወርድ በተደረገ ጥረት ወደታች መውረድ የነበረባቸው ሁለት ክለቦች በሊጉ እንዲቆዩ ተደርጎ አዲሶቹ ከታች ያደጉ ሁለት ክለቦች ተቀላቅለው የፕሪሚየር ሊጉ የክለቦች ቁጥር 16 እንዲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ፌዴሬሽኑ ወስኖ ክለቡ በሊጉ እንዲቆይ ተደርጎ በ1996 ዓም መፕሪሚየር ሊጉ ተሳትፎ በአመቱም ደካማ ውጤት ያስመዘገበበት አመት አሳልፏል፡፡